የአማራ ማህበር በ እስራኤል
የአማራን ህዝብ ጥቅም እናስከብራለን።
ዓላማ
በዚህ በአለንበት ዘመን በተወለድንባት አገር በሙሉ ኢትዮጵያ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካኼደ ያለውን የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ዘመቻ ለመከላከል እና ለማስቆም በመላው ዓለም የሚገኘው የአማራ ወገን እንደሚያደረገው ሁሉ በእስራኤል የሚገኘው አማራም የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይችል ዘንድ መረጃ ማቀበል ፣ ማንቃት እና ማደራጀት ተቀዳሚ ተግባሩ ነው።
የአማራ አንድነት ማሕበር በእስራኤል የሚገኙ አማራዊያንና የአማራ ማህበረሰብን ወዳዶችን በማስተባበር በጠቅላላው የአማራ ሕዝብ ላይ በተጠና መልኩ እየደረሰበት ያለውን ግፍና በደል ያስከተለውን የዘር ማጥፋት እልቂት በማስረዳት ለደርሱት ልዩ ልዩ ጉዳቶችና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማስወገጃ የበኩላቸውን ድጋፍና አስተዎፆኦ እንዲያደርጉ ለማድረግ ሁኔታወችን ማመቻቸት።
በእስራኤል ሃገር ከሚኖሩ ማህበረሰብ እና ከእረጅ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በስደት በመፈናቀል በህልውና ትግል በጦርነት በተፈጥሮ አደጋና በወረርሺኝ የተጎዱትን የአማራ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በገንዘብና በቁሳቁስ እንዲረዱ ማድረግ።
ተልዕኮ
ግብ
በመላው አለም የአማራ ማህበረሰብን ማብቃት
በእስራኤል እና በአለም አቀፍ ተሳትፎ ማህበረሰብን በማጎልበት ጠንካራ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በማጎልበት ለአማራ ህዝብ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ጥቅም እናስከብራለን።
የአለምአቀፍ አውታረ መረባችንን ይቀላቀሉ
ድርጅታችን የአማራ ተወላጆች ደህንነታቸውን እንዲያረጋግጡ በማድረግ ፣ በማደራጀትና በማብቃት የተረጋጋች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ በማስተዋወቅ በቁርጠኝነት የሚሰራ ማህበር ነው።
ያግኙን
የአማራን ማህበረሰብ ለማብቃት እና ተልእኳችንን ለማራመድ ለጥያቄዎች፣ ድጋፍ ወይም ትብብር አግኙን
Connect
+972 54-445-6304
Engage
info@amharaassociationisrael.org