Amhara Association of Israel Media Gallery

የአማራ ማህበረሰብን ማብቃት

ለተረጋጋች ኢትዮጵያ የአማራን ህዝብ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ጥቅም ማራመድ።

በእስራኤል የአማራ አንድነት ማሕበር ዓላማ ተልዕኮ እና ግብ

1ኛ. በጎሳ ፣ በነገድ ከአማራ አብራክ የተገኙ የእስራኤል ነዋሪዎችን በማሰባሰብ በዚህ በአለንበት ዘመን በተወለድንባት አገር በሙሉ ኢትዮጵያ በአማራ ሕዝብ ላይ እየተካኼደ ያለውን የዘር ማጥፋት እና ማጽዳት ዘመቻ ለመከላከል እና ለማስቆም በመላው ዓለም የሚገኘው የአማራ ወገን እንደሚያደረገው ሁሉ በእስራኤል የሚገኘው አማራም የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ይችል ዘንድ መረጃ ማቀበል ፣ ማንቃት እና ማደራጀት ተቀዳሚ ተግባሩ ነው።

2ኛ.በተፈጠሩባት ምድር ፣ ተወልደው ባደጉባት አገር በጅምላ ፍረጃ የጅምላ መጥፋት ፍርድ ተበይኖባቸው በኃይል ለተፈናቀሉትና እየደረሰ ካለው መኣት ለመትረፍ ፣ ለማምለጥ ለሚሸሹትና ለሚሰደዱት ወገኖቻችን የነፍስ አድን እገዛ ማድረግ ነው ።

3ኛ.ተገፊው የአማራ ሕዝብ እየደረሰበት ያለውን ግፍና መከራ ላለንባት አገር ሕዝብ እና መንግሥት ለማሳወቅ መሞከር ነው።

4.ይህ ሰው ሠራሽ ተግባር ያደረሰው ሰቆቃ ከተፈጥሮ አደጋ ጋር በመጣመር ያስከተለው ድርቅ ወገናችን ለረሀብ ፣ለስደት፣ ለመፈናቀል ፣ ለድህነት እና ለመሳሰሉት ሁልቆ መሳፍርት ችግሮች ያጋለጠው በመሆኑ እሱን ለመቅረፍና ቢቻል ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ልዩ ልዩ ድጋፍ ማሰባሰብ እና መርዳት ነው።

5 .በእስራኤል ሃገር የሚገኙ አማራዊያን እና ሌሎች ሰብዓዊ እርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን አፈላልጎ በማስተባበር በአማራ ማህበረሰብ ላይ የተከሰቱ ችግሮችን ለማስወገድ መጣር ነው ።

ዓላማ

ተልዕኮ

በእስራኤል የሚገኙ አማራዊያንና የአማራ ማህበረሰብን ወዳዶችን በማስተባበር በጠቅላላው የአማራ ሕዝብ ላይ በተጠና መልኩ እየደረሰበት ያለውን ግፍና በደል ያስከተለውን የዘር ማጥፋት እልቂት በማስረዳት ለደርሱት ልዩ ልዩ ጉዳቶችና ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማስወገጃ የበኩላቸውን ድጋፍና አስተዎፆኦ እንዲያደርጉ ለማድረግ ሁኔታወችን ማመቻቸት።

ግብ

በእስራኤል ሃገር ከሚኖሩ ማህበረሰብ እና ከእረጅ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በስደት በመፈናቀል በህልውና ትግል በጦርነት በተፈጥሮ አደጋና በወረርሺኝ የተጎዱትን የአማራ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በገንዘብና በቁሳቁስ እንዲረዱ ማድረግ።